Please enter a minimum of 2 characters to search.

Share

Memorial Keepers (1)

Hankins & Whittington Funeral Home

Bekelech Alemu

December 15th, 1948 - April 10th, 2025

Leave a tribute

Memorial

Mementos

                                         የወይዘሮ በቀለች አለሙ የሕይወት ታሪክ።

ቀን፡ ሚያዝያ 5 2017 አ. ም.

 

የወ/ሮ በቀለች አለሙ የህይወት ታሪክ

 

ወ/ሮ በቀለች አለሙ ከአባታቸው ከአቶ አለሙ ይመር እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ጣይቱ ዳቢ ታህሳስ 28 ቀን 1940 አ. ም. በአርሲ ክፍለ ሀገር ልዪ ስሙ ቦሩ አንከቶ በሚባል ቦታ ተወለዱ። በለጋ እድሜአቸው ወላጅ እናት እና አባታቸውን በማጣታቸው ታላቅ ወንድማቸው አቶ ተስፋዬ አለሙ እንደ አባት፡ ታላቅ እህታቸው እማሆይ ጌጤ አለሙ እንደ እናት በመሆን አሳድገው ለቁም ነገር አብቅተዋቸዋል።

 

ወ/ሮ በቀለች አለሙ የዘመናዊ ትምህርት ለመከታተል ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ እያሉ ከልጆቻቸው አባት ከአቶ ተድላ ፋንታዬ ጋር በመተዋወቅ ትዳር መስርተው ከ50 አመት በላይ የትዳር ቆይታቸው ሰባት ልጆች እና አስራ ስድስት የልጅ ልጆች አፍርተዋል።

 

ወ/ሮ በቀለች አለሙ በህይወት ዘመናቸው በጣም ብዙ ውጣ ውረዶችን ያዩ ሲሆን ያጋጠማቸውን ውጣ ውረድ በከፍተኛ ትእግስት በማስተዋል እና በጥበብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ያሳለፉ ጠንካራ ሴት ነበሩ። በተለይ በጣም የሚወዱዋቸውና የሚያፈቅሩዋቸው

የልጆቻቸው አባት አቶ ተድላ ፋንታዬ በደርግ ዘመነ መንግስት ያለ ጥፋታቸው ለመረጣቸው ሰራተኛ ድምፃቸውን በማሰማታቸው መንግስት በ እስራት እንዲቆዩ ባደረገበት ጊዜ እጅግ ከባድ ህይወትን አሳልፈዋል። ልጆቻቸው በትምህርት ተኮትኩተው እንዲያድጉ የተለያዩ አይነት ንግዶችን በመነገድ እንዱሁም የሹራብ ስራ እና የልብስ ስፌት ማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ በመግባት እና በመሰልጠን በዲፕሎማ ተመርቀው ከወጡ በኋላ የልብስ ስፌት እና የሹራብ መስሪያ ማሽኖችን በመግዛት የስራ እድል ለራሳቸው በመፍጠር ችግራቸውን

ተወጥተዋል።

 

 

አቶ ተድላ ፋንታዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ እንደገና ህይወትን እንደ አዲስ ከባለቤታቸውና ከልጆቻቸው ጋር አሳልፈዋል። ከዚያም በ1996 አ.ም አሜሪካ በመምጣት በመጀመሪያ ዋሺንግተን ዲሲ ለሁለት አመት በመቀጠልም ለሃያ ሰባት አመት በኖርዝ ካሮሊና ሻርለት ከተማ ኖረዋል። ሻርለት በቆዩበትም ጊዚ በሻርለት ኤርፖርት እና አዳምስ ማርክ ሆቴል ተቀጥረው በመስራት ባሳዩት ጥሩ ስነ ምግባርና የስራ ትጋት የወርቅ ማእረግ ተሸላሚ ሆነዋል።

ሆኖም ግን ሁል ጊዚ ሀሳብና ምኞታቸው የራሳቸውን ስራ መስራት ስለነበረ “የእናት እንጀራ ” በማቋቋም በብዙ ኢትዮጵያኖች ዘንድ ተወዳጅ እንጀራ ማቅረብ ችለው ነበር።

 

ወይዘሮ በቀለች አለሙ በሃይማኖታቸው በጣም የጸኑ ስለነበሩ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያንን ከባለቤታቸው እንዲሁም ከሌሎች ወዳጆቻቸው ጋር በመሆን ከመሰረቱት አባላት አንዱ ናቸው። እንዲሁም ልጆቻቸውን እና የልጅ ልጆቻቸውን በጥሩ ስነምግባር አንፀው ሀይማኖታቸውን አስጠብቀው የኢትዮጵያን ቋንቋን እና ባህላቸውን አስተምረው የሚያኮራ ስራ ሰርተዋል በሚኖሩበትም ከተማ እንደ አንድ ቤተሰብ በመተያየት ለችግርም ሆነ ለደስታ ደራሽ በመሆን በፍቅር ኖረዋል:: በዋነኝነት በአበረታች ምክራቸው እና ለጋሽነታቸው ይታወቃሉ፡፡ ወ/ሮ በቀለች ከሰው ጋር እጅግ በጣም ተግባቢና ተጫዋች ሳቂታ ለሰው አዛኝ የታመመና የወለደ ጠያቂ በደስታና በሀዘን ጊዜ ከዘመድና ወዳጆቻቸው የማይለዩ እጅግ በጣም ርህሩህ ሴት ነበሩ።

በመጨረሻም ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሚያዚያ 2 ቀን 2017 አ. ም ከዚህ አለም ድካም አርፈው ወደ ሚወዱት ፈጣሪያቸው ሄደዋል።

 

በዚህ አጋጣሚ በእናታችን ህመም ጊዜ ደከመን ሰለቸን ሳትሉ

ከጎናችን በመሆን እናታችንን የጎበኛችኋት እና ያስታመማችኋትን ውድ ዘመድ ወዳጆቻችንን እና አጠቃላይ የሻርለትን ህዝብ በሙሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም ከልብ እናመሰግናለን።

በተጨማሪም የቅርብ የህክምና ክትትል ሲያደርጉላቸው ለነበሩት ዶክተር አምሳሉ እና ዶክተር ለአለም በተለይም በጣም የቅርብ ክትትል ስታደርግ ለነበረችው ኤደን ተድላ ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን::

 

ከልጆቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው

 

የ ሰባት ልጆች እና የ16 ታዳጊዎች አያት ነበሩ።

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በቅዱሳን እቅፍ ያኑርልን። አሜን

 

The Life Story of Mrs. Bekelech Alemu Date: April 13, 2025

 

Mrs. Bekelech Alemu was born on January 7, 1947 in Boru Anketu, Arsi region, to her father Mr. Alemu Yimer and mother Mrs. Tayitu Dabi. She lost both of her parents at an early age and was lovingly raised by her older brother Ato Tesfaye Alemu as a father figure and her elder sister Emahoy Geate Alemu as a mother figure.

 

To pursue a modern education, Bekelech moved to Addis Ababa. While continuing her studies, she met and married Mrs. Tedla Fantaye, the father of her children. They were married for over 50 years and were blessed with seven children and sixteen grandchildren.

 

Throughout her life, Mrs. Bekelech Alemu faced many challenges but overcame them with great patience, wisdom, and resilience. She was a strong woman who never gave up, even when times were difficult. Especially hard for her was the period when her beloved husband, Mrs. Tedla Fantaye, was imprisoned by the Derg regime for his refusal to comply with government demands. During that difficult time, she managed to support her family by engaging in various businesses. She also attended vocational training in tailoring and embroidery, earned a diploma, and eventually bought her own sewing and embroidery machines, creating her own employment opportunities.

 

After her husband was released from prison, they reunited as a family and resumed their life together. In 1998, she moved to the United States. Initially, she lived in Washington, D.C. for a year, and then spent the next 27 years in Charlotte, North Carolina. While in Charlotte, she worked at Charlotte Airport and the Adams Mark Hotel, where she was recognized for her excellent work ethic and received a gold pin as a mark of honor.

 

Still, her dream had always been to run her own business. She founded “Ye Enat Injera” (Mother’s Injera), which became a beloved injera provider among the Ethiopian community.

 

Mrs.Bekelech Alemu was deeply religious and a founding member of Selassie Orthodox Church in Charlotte, along with her husband and close friends. She raised her children and grandchildren with strong moral and spiritual values, teaching them Ethiopian language and culture. She was an active and loving member of the community—present in times of joy and sorrow, and known for her compassion, cheerfulness, wisdom, and encouragement. Sadly, after a period of illness, she passed away peacefully on April 10, 2025, departing this world to join her Creator.

 

On this occasion, we would like to extend our heartfelt gratitude, in the name of the Almighty God, to all our dear relatives, friends, and the entire Charlotte community who stood by us during our mother's illness, visited her, and supported us. We also give special thanks to Dr. Amsalu, Dr. Lealem, and especially Eden Tedla for their attentive and loving medical care.

 

Mrs. Bekelech Alemu was a mother to seven children and a grandmother to 16 grandchildren. 

 

May God rest her soul among the saints.

From her children and family

 

 

We Entrusted Bekelech Alemu's Care To

Hankins & Whittington Funeral Home

Hankins & Whittington Funeral Home

At Hankins & Whittington Funeral Service, nestled in the historic heart of Dilworth, we have provided families in the Charlotte area with customizable memorial services for many years. Our services are crafted to honor your loved ones in ways that are both deeply meaningful and healing. Our rich history began in 1946 when Irvin W. Hankins and James B. Whittington took the reins of the Crouch Funeral Home. The growth of our service and the community's support led to our move in March 1963 to the current location—once St. Luke’s Lutheran Church, built in 1930. Our chapel, a cherished historic landmark within the storied Dilworth neighborhood, is renowned for being the only funeral home in Charlotte graced with its own chapel, echoing with decades of history and serenity....

Learn more

(704) 218-9955

Tributes

Share a favorite memory, send condolences, and honor Bekelech’s life with a heartfelt message.

Customize Cookie Preferences

We use cookies to enhance browsing experience serve personalized ads or content, and analyze our traffic. By clicking 'Accept All', you consent to our use of cookies. Learn more on our Privacy Page